colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ቅዱሳን አባቶች

ቅዱሳን አባቶች በገዳም ያላችሁ ሰላምን አሠጡኝ ከፈጣሪ አስታርቃችሁ በሀገራችን ላይ ይደር በረከት ጸጋችሁ አምላክ በበደላችን በእኛ እዳይከፋ ምልጃችሁ አይለየን በኃጢአት እንዳንጠፋ ሰላም ለእናንተ ይሁን ቅዱሳን አባቶች ከዓለም ርቃችሁ በጾም ጸሎት የጸናችሁ በገድል በትሩፋት ዲያብሎስን የረታችሁ ቅዱሳን አባቶች በእኛ ላይ ይደር ጸጋችሁ ውርጭ ሀሩሩን ሣትሰለቹ በጸሎት የጸናችሁ በረከታችሁ በእኛም ይደር በልጆቻችሁ ጸጋችሁ ብዙ ነው ጸሎታችሁ ኃይል ያደርጋል ከጥፋት ጠብቆ አጋንንትንም ይዋጋል የእናንተን ጽናት አይቶ እኛንም ታግሶናል በኃጢአት ስንረታ በምሕረት ጎብኘቶናል