በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል/2/ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል/፪/ ናቡከደነፆር ጨካኙ ንጉሥ በባቢሎን ሀገር ጣዖት የሚያነግሥ እያለ ስገዱ አማኙን ሲያምስ ወጣቶች ተነሡ በቅናት መንፈስ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል/2/ ለሠራኸው ጣዖት አንሰግድም እያሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ሞሉ የፈጠረን አምላክ ያድናል ሲሉ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /2/ አዘ ------------ ነበልባል ነዲዱ እንዲያቃጥላቸው በጭካኔ መንፈስ አስወረወራቸው ገብተው ሲጸልዩ ፍህሙ ሳይነካቸው መልአኩን ልኮ አበረደላቸው ገብርኤል /2/ በመስቀል /2/ እንደ ሦስቱ ሕፃናት በእምነት ለሚቆመው መልአኩን ይልካል እግዚአብሔር ሊረዳው እሳቱም ይበርዳል መልአኩን ሲልከው ገብርኤል /2 /በመስቀል በእምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል/፪/ አናንያ አዛርያ ሚሳኤል/፪/