ጊዮርጊስ ብርሃኑን አበራ/2/ ዱድያኖስ አፈረ ከጣኦቱ ጋራ ጊዮርጊስ ብርሃኑን አበራ /2/ ለዲያብሎስ ያልሠገደ ጀግናው ጊዮርጊስ ደግሞ በዓይን ታየ ክብሩ ሲወደስ ከሞት አፍ ያወጣት ቤሩታይትን በሰማእቱ ገድል ድል ሆነ ሠይጣን ቅዱሱ ሰማእት ጊዮርጊስ አባታችን አሳየ ሥልጣኑን ከሞት እንደሚያድን መድኃኒት ክርስቶስ የገለጠው ብርሃን እኛም እንድንድን ከዘመኑ አውሬ እስቲ እንግለጽለት ክብሩን በዝማሬ ተዋሕዶ አበራ ደግሞ እንደገና ደራጎን ድል ሆኖ ሞቶ ቀርቷልና ለአሸናፊ ጌታ ለእግዚአብሔር ልኡል ምስጋና እናቅርብ እንበል እልል ጊዮርጊስ አበራ ብርሃን/2/ ሰው በላውም አውሬ ሞተ ደራጎን/2/ ጊዮርጊስ አበራ ብርሃን