መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ /2/ መንገድ ጠረገ ለኢየሱስ መምጫው ሊደርስ ተክለሃይማኖት በጸሎት/2/ ተክለሃይማኖት በጸሎት የእኛ አባት ገብረመንፈስቅዱስ ሐዋርያ /2/ ከንሒሳ መጥተው ጸለዩላት ለኢትዮጵያ ዜና ማርቆስ በጽኑ እምነት/2/ ፀሐይ አቆሙ እንደ ኢያሱ በደብረ ብስራት/2/ እመቤታችን ድንግል ማርያም /2/ ምሕረት አሰጭን ከመለኮት ከመድኃኔዓለም መሰቀሉን ይዞ በፈረስ/2/ ከዘንዶ አስጣላት ቤሩታዊትን ቅዱስ ጊዮርጊስ