አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማእት /2/ ምሕረት ለምኝልኝ ከዓለም መድኃኒት የዓለም አሽንክታብ ሳይስብሽ ጽድቅን የመረጥሽ የጌታ አገልጋይ አርሴማ ቅድስት አንቺ ነሽ መስቀል ተመርኩዘሽ በዓላማሽ የጸናሽ አርሴማ ቅድስት ተቀዳጅተሸ አክሊል ሙሽራ ሆነሽ ሰማእት የዚህ ዓለም ደስታ ርስት ጉልት ንብረት ሣይሰብሽ ዘላለማዊ ሕይወት ክብር ጸጋ ስለመረጥሽ የዓለም መድኅን አማኑኤል በእውነት አከበረሽ በእግዚአብሔር ዘንድ በፍቅር/2/ አድገሽ የሰማእታት አክሊል በረከት ሆነሽ ተሸላሚ አዝ --------------