መጽሐፈ ዜናሁ ለቂርቆስ መንፈሳዊ ወዘመንክሮ ሰላም/2/ ጸሐፍ ውስተ ልብየ/2/ እንዘ ትገብር ከለመ ደመከ አምላካዊ በመስቀል ዘዘነበ/2/ እንተ ቅዱስ ቂርቆስ ሕፃን ለአምላክ ሆንክ ምስክር/2/ በእኛም ልብ ጻፍልን /2/ የአምላክን ፍቅር/2/ በእስክንድሮስ ዘመን ነበርክ ታላቅ አስተዋይ ሕፃን አምላክህም ሰጠህ /2/ የክብር አክሊልን/2/ ያ ሁሉ መሣሪያ ሣይስፈራህ የመሠከርክ የአምላክን ክብር ድንቅ ነው የአምላክ ሥራ/2/ ለዚህ ሕፃን ሰጠው እንዲኖር ሣይፈራ/2/ አትፍሪ እዳልካት እናትህን እኛንም አድነን ከመከራ/2/ እንድንድን ርዳን ከዲያብሎስ ጭፍራ በጽድቅህ አድለን እንኑር በሥራ/2/