ከጌ ዬ ፍቅር የሚለየኝ ማን ነው /2/ መከራ ችግር ሥቃይ ወይስ መራቆት ነው /2/ አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም /2/ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም /2/ የሰማይ ቤ ችን አማኑኤል የሠራው /2/ ግንቡ ንጹሕ ውኃ መሠረቱ ደም ነው /2/ ሳይነጋ ተራምደን እንግባ ቤ ችን /2/ በደሙ መሥርቶ ከሠራልን ቤት /2/ ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት /2/ የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት/2/ የውኃ ግድግዳ የደም መሠረት /2/ ይኸው እዚህ አለ የሥላሴ ቤት /2/ ጠላት ቢተባበር ዲያብሎስ ቢያብር /2/ ሊለየን አይችልም ከእግዚአብሔር ፍቅር /2/