እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ/2/ ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/ ጌታ አለ ብለን ደስ ብሎን ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን/2/ ድንግል አለች ብለን ደስ ብሎን አበባዮሽ ቅድስት/2/ ባለእንጀሮቼ ቅድስት ቁሙ በተራ ›ቅድስት › በጎ ምግባርን ››ቅድስት በእምነት እንሥራ ቅድስት ›› ዛሬ ነው ቀኑ ቅድስት › መመለሻችን ቅድስት ›› ይቅር እንዲለን ቅድስት ›› ቸሩ አምላካችን ቅድስት ›› አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/ ድንግል ማርያምን ቅድስት እንለምናት ቅድስት ምሕረት የሚያሠጥ ቅድስት ቃልኪዳን አላት ቅድስት ጭንቀት ይርቃል ቅድስት ይቀርባል ሰላም ቅድስት ስሟ ሲጠራ ቅድስት የድንግል ማርያም ቅድስት አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ በራ/2/ በሕገ ልቡና ጥንቱን ፈጣሪን አውቀሸ ጥንቱን ሕገ ነቢያት ከዓለም ቀድመሽ ተቀበልሽ ከዓለም በብሉይ ኪዳን ለጌታ መሥዋእት አቀረብሽ ለጌታ ተስፋ ካደረጉት ከአይሁድ ከእስራኤል ቀድመሽ ከአይሁድ ሕገ ወንጌልን በፊት ይዘሽ ተገኘሽ በፊት ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ጸጋ አለሽ/2/ ስለፈጸምሽ ሦስቱን ሕግጋት የፈጣሪሽን ካለፈው ስህተት ሁላችን እንድንመለስ ሁላችን አዲሱ ዓመት ለሁሉ መጣ ማቴዎስ ለሁሉ ይህም ያልፍና በጊዜ ይመጣል ማርቆስ በጊዜው ሌላው ይተካል በጊዜው ዘመነ ሉቃስ በጊዜው ወልደ ነጎድጓድ በጊዜው ሲደርስ ዮሐንስ በጊዜው በየዓመቱ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ አደይ የብርሃን የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ አበራ2/ ኢትዮጵያ ባህል ቋንቋሽ የሚያኮራሽ/2/ ዘመኑ አልፎ ቅድስት ሲሄድ ማቴዎስ ቅድስት አዲሱ ዘመን ቅድስት ሲመጣ ማርቆስ ቅድስት እድሜን ጨምሮ ቅድስት ለሠጠን ጤና ቅድስት ለመድኀኔዓለም ቅድሰት ይድረስ ምስጋና ቅድስት አደይ የብርሃን ጮራ በማርቆስ በራ እቴ አበባ እቴ አበባዬ አዬ ቅድስት እናቴ እቴ አበባ ስትለኝ ከርማ አዬ ቅድስት እናቴ መከረችኝ ደግማ ደጋግማ አዬ ቅድስት እናቴ ቃሉን ሰማው አድምጥው ብላ እዬ ቅድስት እናቴ አዬ ቅድስት እናቴ አዬ ቅ. እናቴ/2/ ይሸታል የእጣኑ ጢስ ሲታጠን ከመቅደሱ በመላእክት ዜማ ካህናት ሲቀድሱ ሲታጠን ከመቅደሱ/2/ ከብረው ይቆዩን ከብርው ከዓመት አውደ ዓመት ደርሰው በእምነት በምግባር ጸንተው ነጽተው ንስሓ ገብተው ለሥጋ ወደሙ በቅተው ከብረው ይቆዩ ከብረው ከብረው ይቆዩ ከብረው ከዓመት እከሰ ዓመት ደርሰው ቅን ታዛዥ ልጅን ወልደው ትኁት ሠው አክባሪ ሆነው የፍቅርን ሸማ ለብሰው ከብረው ይቆዩ ከብረው አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም ኢትዮጵያ እንዳንቺ የለም አበባው ለምለም ቄጤማው ለምለም ተዋሕዶ እንዳንቺ የለም አበባው ለምለም ድንግል ማርያም ያለአንቺ እመቤት የለም