የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት ድንግልን ከመሐል ሚካኤልንከፊት አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት እዩ ተመልከቱት የሰማዩን አባት /2/ የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ታላቅ ክብር ሊያዩ የታደሉ በጽድቅ ሥራቸው ደምቀው ይ ያሉ /2/ አዝ . . . የቅዱሳን ኅብረት የቅዱሳን ሀገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር ጽድቅና ርኅራኄ የተሞላ ሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ /2/ አዝ . . .