ምንም ሳትበድል ኃጢኣት ሳይኖርባት አንድዬ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት ሀገር እንደሌለው ከሀገር ሲያሳድዳት ምን በድላ ይሆን ምን ኃጢኣት ኖሮባት የአዳም መዳኛ ድንግል ማርያም አንድ ልጇን ይዛ ካረች በዓለም /2/ ሄድሮስ ምቀኛ የዲያብሎስ ወዳጅ ሊገድለው አስቦ የድንግልን ልጅ መኟ ለእርሷ አዘነ ጨከነባት እንጂ ስትሆን ለፍጥረት የዓለም አማላጅ አዝ ------------- የሲና በረሃ እግሯን እየፈጀው አንጀቷ ተርቦ ውኃ ጥም ሲፈጀው መኟ ለእርሷ አዘነች የርሷን መንገላት ሐሰቧ ለእርሱ ነው እንዳይገድሉባት አዝ ------------- አቤት መከራሽ አቤት ስደትሽ እኔ ልኝፈለው ወራዳው ልጅሽ መሰደድ ያለብኝ እኔ ነበርኩኝ የእግዚአብሔ@ርን ትእዛዝ የተላለፍኩኝ አዝ -------------