ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/ ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን ለዚህ ድንቅ ውለታው ምስጋና ያንሰዋል በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/ ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን ከአለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል ፍቅርህ የበዛልህ ምን ልክፈልህ ጌታ ስምህን ላመስግነው ከጠዋት እስከ ማታ ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/ ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን በቃዴስ በረሀ ምንም በሌለበት በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት ልባችሁ አይፍራ በፍፁም እመኑት ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/ ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/ ለታላቁ ክብር ለዚህ ላበቃን ከሞት ወደ ሕይወት ላሸጋገረን ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ደበለን የሐና የኢያቄም የእምነታቸው ፍሬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ የኢያቄም ስዕለቱ የሐና እምነት ለምኝልን ለኛ ኪዳነ ምሕረት