እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለምና እልል በሉ ቁሙ ለምስጋና/2/ አዝ --- ባሕር ተከፈለ እሲኪታይ መሬቱ ፈርኦን ወደቀ አልሠራም ትምክህቱ ደካሞቹም ጸንተው ተራመዱ ኃይለኞቹም ይኸው ተዋረዱ አዝ --- የኢያረኮ ቅጥር የማይደፈረው ይኸው ፈራረሰ የሰው እጅ ሳይነካው ኃይለኞቹም ቢበረታቱብን እንጸናለን በእርሱ ተደግፈን አዝ --- የተወረወረው የጠላታችን ጦር ሜዳ ላይ ወደቀ ጋሻ ሆኖ እግዚአብሔር ለሥላሴ ይድረስ ምስጋናችን ተሸነፈ አዳኝ ጠላታችን አዝ --- ባሕር ላይ ሲራመድ ሞገስ አለው እርሱ በግርማው ሲነሳ ጸጥ ይላል ነፋሱ የድንግል ልጅ እኛ የምናመልከው ከሀሊ ነው የለም የሚሳነው