እንደ አባቶቻችን እናቅርብ ምስጋና ስሙን ለማመስገን ተፈጥረናልና/2/ ዲቦራና ባርቅ ማለዳ ሲቀኙ ለምስጋና ቆመው ከአምላክ ሲገናኙ የአሳፍም ልጆች ጸናጽሉን ይዘው ይዘምሩ ነበር በአንድነት ሆነው የዚህ ዓለም ጉድፍ ያልተጨመረበት ንጹሑን ምስጋና ለአምላክ እንሰዋለት በሰዓትት በማኅሌት ያሬዳዊ ዜማ እንዘምር ሁላችን ድምጻችን ይሰማ በምስጋና እንቅረብ ወደ ሰማዩ ክብር ዳዊት በሃይማኖት ባለበት ማኅበር ከበሮ ይመታ በገና ይደርደር ለስሙ እንቀኝ በምሥጢር እንዘምር የሰማይ ካህናት ሲዘምሩ አይቶ ምሥጢር ተገልጾለት በመንፈስ ተቀኝቶ በመዝሙረ ዳዊትን ሐዲስና ብሉይ ይዘምር ነበረ ያሬድ ማኅሌታይ