colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

እልል በሉ

እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን/2/ ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም/2/ ሕይወቱን የሠዋ እንደ አምላክ ማን አለ ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋር /2 ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን ለማይነገረው ለአማላክ ስጦታ ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ