እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት እግዚአብሔርን አመስግኑት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት ሰማይን ያለምሰሶ ምድርንም ያለመሠረት ያጸናው እርሱ ነው ሥራህ ድንቅ ነው በሉት የባሕርንም ጥልቀት የመጠነ ዳርቻዋን የወሰነ እግዚአብሔርን አመስግኑ ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት ማእበል ነፋሱን የሚገስጽ ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት ንጹሐ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ የነገሥታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ ዘለዓለም እርሱ ነው የማይለወጥ እግዚአብሔር ሥራህ ድንቅ ነው በሉት ጥበብን የሚሰጥ ጥበበኛ ፍርድ የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም እግዚአብሔር ግሩም ነው ለዘለዓለም