የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው ብዘምርለትም ያንስበታል ይኸው ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝከኝ ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ በኢያሪኮ መንገድ ስለምን ቁጭ ብዬ ብርሃን እጅግ ናፍቆኝ ከሰው ተገልዬ የብርሃን ጌታ ወደ እኔ መጣና ዓይኔን አበራልኝ በእጁ ዳሰሰና የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው ብዘምርለትም ያንስበታል ይኸው ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝከኝ ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ ለብዙ ዘመናት አልጋ ላይ ተኝቼ የሚረዳን አጣሁ ጠሉኝ ዘመዶቼ የኔ ጌታ አምላኬ ወደ እኔ መጣና አልጋህን ተሸከም አለኝ ፈወሰና የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው ብዘምርለትም ያንስበታል ይኸው ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝከኝ ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ አስራ ሁለት ዓመት ደም እየፈሰሰኝ ምራቅ እየተፉ ሁሉም ሲያንቋሽሹኝ የጌታዬን ልብሱን ጫፉን ብዳስሰው ኃይልም ከእርሱ ወጣ ደሜን ቀጥ አረገው የወደደኝ ጌታ ምን አድርጌለት ነው ብዘምርለትም ያንስበታል ይኸው ከውድቀቴ አንስተህ ድካሜን ያገዝከኝ ሰባራውን ድልድይ ገጥመህ ያሻገርከኝ ሰካራም ዘማዊ ወንበዴ ነበርኩኝ የዓመጸኞች መሪ ደምን ያፈሰስሰኩኝ ዛሬ ግን ታሪኬን ጌታ ቀይሮታል ለኃያሉ ጌታ ምስጋና ይገባል