colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ለእኔስ ወደ እግዚአብሔር

ለኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል /2/ መታመኛዬ እርሱ ነውና ይገባዋል ክብርና ምስጋና ፍቅሩን እያሰብን እንቅረብ ወደ እርሱ ይምረናልና መሐሪ ነው እርሱ መልባችን ይንገሥ ይግባ ከቤታችን የሕይወታችን ዋልታ እርሱ ነው ተስፋችን /2/ ለኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል /2/ መታመኛዬ እርሱ ነውና ይገባዋል ክብርና ምስጋና ከቶ አላገኝም እርሱን የሚመስል ነፍሴን የሚያከብራት የሚሰጠኝ ሃይል በመከራ ሰዓት ከክፉ የሚያድነኝ ከየት አገኛለሁ መጠጊያ የሚሆነኝ /2/ ለኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል /2/ መታመኛዬ እርሱ ነውና ይገባዋል ክብርና ምስጋና የለመለመ መስክ መሸሸጊያዬ ነው በሰላም ወጥቼ ሰላም እገባለሁ ተስፋዬ እርሱ ነው ይጠራኛልና ዘወትር አቀርባለሁ ክብርና ምስጋና ዘወትር አቀርባለሁ ለአምላኬ ምስጋና ለኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል /2/ መታመኛዬ እርሱ ነውና ይገባዋል ክብርና ምስጋና እኔስ ይሻለኛል መቅረብ ወደጌታ ጋሻዬ ነውና የነፍሴ አለኝታ ስለዚህ እቀርባለሁ አልርቅም ከደጁ ጠግቤ እኖራለሁ በበረከት እጁ /2/