በገና አንሥተን መሰንቆን እናመስግነው ስምህን አንደ አምላካቸን ማንም የለም ይክበር ይመስገን ለዘለዓለም/2/ ዓለም ሞኝነት ይመስለዋል ለአንተ መንበርከክ ይከብደዋል ፍቅርህን ቀምሰን ዝም አንልም እንዘምራለን ለዘለዓለም/2/ ሞኝነት ለእኔ መች ሆነና ፊትህ ያቆመኝ ለምስጋና እንድቀኝልህ ግድ የሚለኝ ፍቅርህ ብቻ ነው የማረከኝ/2/ ፈውስን ስትሰጠን ስትባርከን ፍቅርህን ልከህ ስትጎበኘን ጉልበት ይጸናል በአንተ ጸጋ ማነው የሚከፍልህ የአንተን ዋጋ ስንዘምርልህ የሚስቁ ብዙ ሜልኮሎች ዛሬም አሉ የእኛ የሆነ ምንም የለም አምላክ ስላንተ ዝም አንልም/2/