በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ለገለጸው ምን ስጦታ አለን ለእርሱ የምንከፍለው ምስጋና ነውና ከእኛ የሚፈልገው ቸሩ አምላካችንን ተመስገን እንበለው ዓለም እስኪደነቅ ድንቅ አድርጎልናል እንዲህ ያለዋጋ ጸጋውን ሰጥቶናል ትናንት ለእስራኤል ሞገስ የሆናቸው ስሙን እናመስግን ዛሬም ከእኛ ጋር ነው አፋችን ይመላ በታላቅ ምስጋና ከኃጢአቱ ባሕር ተሻግረናል ክቡር ሞስጉን አምላክ ቅዱስ እንበለው ኢሳይያስም በክብር በራእይ እንዳየው ከቶ ለእግዚአብሔር ምን ይከፈለዋል ሁሉም የራሱ ነው ማን ምን ይሰጠዋል አምስጋኝ ቢቀኝም ክብር ላራሱ ነው እርሱ በባሕርዩ ዘለዓለም ምስጉን ነው ሙሴም ዝም አላለም ዳዊትም አልተኛም በጎቹ ዘመሩ ለመልካሙ እረኛ ያሬድ ተመሠጠ ወደ ሰማይ ዓለም እኛም ከእነርሱ ጋር እንዘምር ዘለዓለም