ሳይገባኝ አምላክ ሳይገባን ለዚህ ያደረሰከኝ እኔ ማነኝ/2/ ምን ያላደረክልኝ አለ ጌታ ለእኔ ምንም ባሳዝንህ በምግባሬ ኃጢአቴን ተመልክተህ ቸል ያላልከኝ በሕይወቴ ብዙ ነገር ሠራኸልኝ ውለታህ ብዙ ነው የአንተ ወሰን የለው ተናግሬ እኔስ አልጨርሰው ውድቀቴንም ድክመቴንም እኔ አውቃለሁ የጠበቀኝ ቸርነትህ ምሕረትህ ነው ለማይነገረው ፍቅርህ ግሩም ሥራህ ልጆችህን የምትጠብቅ ከመከራ ምን እንመልሳለን ለአንተ ለአምላካችን ከመዋረድ አድነኸን ላከበርከን