ዘመኔ በከንቱ እንዳይፈጸም መልካም እንድሠራ አርዳኝ መድኃኔዓለም ኃጢአቴ በዝቶብኝ መኖር አቅቶኛል በቤትህ ውስጥ ልጣል ሰላም ይሻለኛል ድንገት ስትጠራኝ ግራ እንዳይገባኝ በሕይወት ዘመኔ ለንስሓ አብቃኝ አንተ የወሰንከው እድሜዬ ሲያበቃ ለነፍሴ የሚቆም አድለኝ ጠበቃ/2/ በሞት ሣልገታ ሳይደክሞ ጉልበቴ እንደምትወደው ልኑር መድኃኒቴ በሰማይ መንግሥትህ አስበኝ አደራ አቁመኝ በቀኝህ ከቅዱሳን ጋራ /2/