እግዚአብሔርን ጠራሁት በኀዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት በጭንቀቴ ጊዜ አወጣኝ ከጭንቀት ከሐዘን ከትካዜ /፪ የልመናዬን ድምጽ እርሱ ሰምቷልና ጆሮውን ወደ እኔ አዝንብሏልና በዘመኔ ሁሉ ስጠራው እኖራለሁ ጎስቋላ ብሆንም ምስጋና አቀርባለሁ/፪/ እንደ ቃልህ መጓዝ መራመድ አቅቶኝ የኃጢአቱ መንገድ ማእበሉ ገፍቶኝ ወደ እርሱ ስማጸን ደግሞም ስጸጸት አላሳፈረኝም መጣ በምሕረት /፪/ በበዛው ምሕረቱ ያለፈውን ትቶ በፍቅሩ ጎበኘኝ አልተወኝም ከቶ ሊቀበኝ ወዶ ፊቱን አበራልኝ ማን ይቃወመኛል እግዚአብሔር ካለልኝ/፪/ ኖኅን አንዳዳንከው እኛንም አድነን ከቀስቱ እንድናመልጥ ምልክትን ስጠን በትርህ ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑን አንተ ከእኛ ጋር ነህ አንፈራም ክፉውን/2/