ተነሡ እንዘምር በአንድነት ሆነን በእልልታ/2/ ኸኸኸ ምስጋና በሰማይ ምስጋና በምድር /2/ ለኃያሉ ጌታ ለልኡል እግዚአብሔር አስፊሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር ሁሉንም አለፍነው እግዚአብሔር ይመስገን ሕዝቦች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሶአል አምላክ ሆይ ስምህን ብንጠራው /2/ አልጠገብ አለ ምንኛ ጣፋጭ ነው አቤት ያንተ ሥራ ያንገተ ልግስና ቢነገር አያልቅም ስምህ ነው ገናና ሰማይ ዙፋንህ ነው ምድር መረገጫ በዚህም በዚያም ቢሆን በሁሉም አንተ ነህ በሄድንበት ሁሉ ትከተለናለህ ከእንቅፋት ከድንጋይ ትሰውረናለህ ስለመልካም ሥራህ አለብን ውለት ሰለማይነገረው የማዳን ስጦታ ተመስገን እንበል ከጠዋት እስከማታ ሌላ ምንም የለም የምንከፍለህ ጌታ መልስ እንድናዘጋጅ ቶሎ ሳንጠራ ሳለ አንደበታቸን ምስጋናህን ያውራ ምስጋና በሰማይ ምስጋና በምድር እስከ ዘለዓለም ለስምህ እንዘምር አዝ ---