ለምትቀር ዓለም/2/ ለምትቀር ዓለም መታከት መድከም በዓለም በረሀ ወድቀን እዳንጠፋ መጽናት ገባልናል በፍቅር በደስታ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህን ይዘን ድል ማድረግ አለብን የምትቀር ዓለምን አዝ --- በሥጋዊ ምኞት በዓለም ተጠምደን የአምላካቸንን ትእዛዙን ጥሰን ከፈጣሪያችን ፊት ከቤቱ እንዳንጠፋ ወላዲተ አምላክ አንቺ ሁኝን ተስፋ አዝ --- በሲኦል በረሀ እንዳንቀር ወድቀን ልንቆም ይገባናል በእምነት ተደግፈን ጌታችን ሲመጣ በግራ ከመቆም ካሁኑ እንዘጋጅ ነገ የእኛ አይደለም አዝ --- እንደ ሰማእታት ዓለምን በመናቅ ጽድቅን እየሠራን ከክፋት በመራቅ እንዘን አናልቅስ ስለበደላችን በቀኙ እንዲያቆመን ቸሩ ፈጣሪያችን አዝ ---