ጌታ ሆይ ለስምህ እዘምራለሁ ልኡል ሆይ ለክብርህ እልል እላለሁ በአንተ ደስ ይለኝል ሐሴት አደርጋለሁ /2/ የበዛው ምሕረትህ በእኔ ላይ ተገልጦ የትናንቱ ስሜ በአንተ ተለውጦ ሞገስ ስለሆንከኝ ከፊትህ ቆሜያለሁ በአውደ ምሕረትህ ስምክን እጠራለሁ ያለቀውን ነገር የተቆጠረውን ትቀጥለዋለህ ለአንተ አይሳንህም መቃብሩን ከፍተህ መግነዝ የምትፈታ የሞትም ጌታ ነህ የድሆች አለኝታ አንተ የመረጥከውን ማነው የሚከሰው ያከበርከውንስ ማነው የሚቃወመው በሰው ፊት የሚታይ ደም ግባት ባይኖረኝ ጸጋህ ይበቃኛል እዘምራለሁኝ እኔስ ቀንቻለሁ አምላኬ ለክብርህ በልቡናዬ ውስጥ እስኪሳል መስቀልህ የተጋረደውን አዚሙን አጥፋልኝ ውለታህን አውቄ በአንተ ደስ እንዲለኝ