ዓይኖቼ ማዳኑን አይተዋልና/2/ ይገበዋል /2/ ክብርና ምስጋና ከሰማይ ወረደ ሰውን በማፍቀር ኃያሉ ጌታቸን ቸሩ እግዚአብሔር በቤቴልሔም ዋሻ በዚያ በግርግም ተወለደ ዛሬ መድኃኔዓለም የተነበዩለት ብዙ ነቢያት ከድንግል ተወልዶ አዳነን በእውነት ከበደል ጉራንጉር አነሣን ከትቢያ በአንድነት እንዘምር እንበል ሃሌ ሉያ የተናቅን ስንሆን እኛን ሊያከብር ወድዶ በፍቅር አከበረን እራሱን አዋርዶ ምን አይነት ፍቅር ነው ፍጹም ምሕረት የአምላክ መወለድ በከብቶች በረት በንጽሕና ጸንተሸ ቤተ መቅደስ የኖርሽ በኅቱም ድንግልና መድኃኒትን ወለድሽ የዓለምን ኃጥአት የሚያስተሠርይ ጌታ ተወልዷል ከድንግል የሰዎች አለኝታ