አደርገህልኛለና በቸርነትህ/2/ አመስግንሃለሁ እልል እልል /2 ለዓለም ዓለም አማኑኤል እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም /2/ ቀኑ ጨለሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ የችግር አረንቋ ፊቴ ተደኩኖ ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ ፈጽሞ አራቅኽልኝ የልቤን ትካዜ አዝ --- አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ አዝ --- ጥቂትዋን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ መንክር ለባሕርይህ እጹብ ለአንተ ሥራ አዝ --- አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሠጥሃል ድሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና ማሠሮዬ ሞልቷል አይጎል እንደገና አዝ ---