የነገሥታት ንጉሥ ቸሩ አባት የጌቶቹም ጌታ በሰማያት ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/ አዝ --- ቅዳሜ በአንተ ዘንድ ቸሩ አባት /2/ ምንም ቦታ የለው በሰማያት ፍጹም ቸርነትህ ቸሩ አባት የአንተ ባሕርይ ነው በሰማያት ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/ አዝ --- ምሕረትህ ለሰው ልጅ ቸሩ አባት እጅጉን በዝታለች በሰማያት ኃጢአት በበዛባት ቸሩአባት ጸጋህ ትበዛለች በሰማያት ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/ አዝ --- የትእግሥት ብዛት ቸሩ አባት እኔን ድንቆኛል በሰማያት የኃጢአቴን ዋጋ ቸሩ አባት መቼ ከፍለኸኛል በሰማያት ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/ አዝ --- ስንበድል ስንቀጥፍ ችሩ አባት አንተ ተደብቀን በሰማያት አይተህ እንዳላየህ ችሩ አባት በምሕረት አለፍከን በሰማያት ከቶ እንደአንተ ማነው ሩኅሩኅ አባት/2/ አዝ ---