አድፈኒ እምተ ሰጥሞ ኪያየ ክቡድ/2/ ናሁ በላእሌየ ተንሥአ ምገድ/2/ ሞገድ ናሁ በላእሌየ ተንሥአ ሞገድ አድነኝ እንዳልጠፋ በኃጢአት ወጥመድ /2/ እነሆ በእኔ ላይ ተነሥቶአል ሞገድ /2/ አድፈኒ ከገሃነም እሳት ጠፍቶ ከማይጠፋው ከዚያ አስፈሪ አውሬ ከሚንቀላፋው ከሰይጣን እሥራት ከዳግመኛ ሞት እግዚአብሔር ሆይ ርዳኝ እንዳልቀር ከቤትህ አዝ --- አድፈኒ ማእበሉ አወኮኝ እንዳልንገላታ ሞገድ እንዳይጥለኝ ርዳኝ የእኔ ጌታ ከክፉ ፈተና ከምማረርበት ከዝሙት ከርኩሰት ፍቅር በሌለበት አዝ --- አድፈኒ ከሐሜት ከስርቆት ከኃጢአት ባርነት ከጨለማ መንገድ ሕይወት ከሌለበት ከድፍረተ ኃጢአት አምላክ ከሚያዝንበት ከተንኮል ከበቀል ቁጣ ከበዛበት አዝ --- አድፈኒ ዛሬ ካለሁበት ከኃጢአት ወጥመድ በዚያ በምጽዓት ቀን በእኔ ከመርፈድ የኃጢአት በሽታ አዳልጦ እንዳይጥለኝ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አደራ ደግፈኝ አዝ ---