ስምህ በሁሉ ተመሰገነ ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ አንተን ማወደስ ያስደስተናል ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል አምላክ ተመስገን በሰማያት ስምህ ይወደስ በፍጥረታት ከሕፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ/2/ በምግብ እጦት ብንሰቃይም ማኅሌትህን አናቋርጥም የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም እንዘምራለን ለአምላካችን ስም/2/ ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣ ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም ቸርነትህን እንጠብቃለን ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን/2/