አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዓይኔ በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ የአናብስትን አፍ በኃይሉ የዘጋ የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኔ ጋር በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ ለጌታዬ ክበር እዘምራለሁኝ አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም ለጣኦት እንድንሰግድ ነገሥታት ቢያውጁም ሁሉ ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም ጽናት ይሆነኛል ጌታ መድኃኔዓለም