አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋር አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ ከቅዱሳን ጋራ ልዘምር አብሬ እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም ለጣዖት እንድሰግድ ነገሥታት ቢያውጁም ሁሉ ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም ከእኛ ጋር ይሆናል አምላክ መድኃኔዓለም አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዐይኔ በገባኦን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ ከኃጢአት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛ ጋር