እግዚአብሔር ሆይ የሚረዳን የለምና ከኛ አትራቅ ተስፋችን ነህና አንተን አምነን ስንጠራህ አትለየን አምላክ ሆይ ጠብቀን አዝ --- በአንተ ታምኛለው ዘላለም አልፈር በጽድቅ ልመራ በፍቅር እንድኖር ጆሮህን አዘንብልህ ፈጥነህ አድነኝ መንገዴን አቅንተህ በሕይወት ምራኝ አዝ --- አምባና መጠጊያ መሸሸጊያ ሁነኝ በድካሜ ጊዜ የለም የሚረዳኝ የእውነት አምላክነህ አቤቱ ተቤዥን ከአንተ በቀር ለእኛ ምንም ተስፋ የለን አዝ --- የሕይወቴ ብርሃን መታመኛዬ ነህ ዝም አትበለኝ አንተ አቤቱ ስጠራህ በመከራዬ ቀን አቤቱ ሠውረኝ በቃልህ እንድኖር በምሕረትህ ጎብኘኝ አዝ --- እንዳሽንፍ እርዳኝ የዓለምን ፈተና ጠላቴ እንዲያፍር በእምነት እንድጸና አንተ ተዋጋና እንዳልወድቅ እርዳኝ ከጎኔ አትለየኝ ብርታትን ስጠኝ አዝ ---