ብርሃን የለበሰው በሰማያት ያለው/2/ እንደ እግዚአብሔር ከቶ ማንም የለም/2/ ውኆችን በእፍኙ የሠፈረ ተራሮችን በሚዛን የመዘነ ሰማይን በስንዝር የሚለካ ዘመንን በዘመን የሚተካ/2/ አዝ --- ከዓለም በፊት የነበረ ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ በምድር ክብብ የሚቀመጥ ሁሉን ሲለውጥ የማይለወጥ /2/ አዝ --- ዙፋኑ የጸና በሰማይ ሁሉ የሚቻለው አዶናይ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የሌለው አልፋና ኦሜጋ አምላክ ነው/2/ አዝ --- ከሀሊ ኩሉ ሁሉንም የሚያውቅ ፈታሄ በጽድቅ ሥራው ረቂቅ ዓለምን የመላ ፈጥሮ የሚገዛ መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ/2/