አሁንስ ተስፋ ማነው/2/ እግዚአብሔር አይደለምን /2/ በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን ጠበቅህ ለአፌ ጠባቂ እንዳለ አውቅሁ ከኃጢአቴ ሁሉ አንተ አድነኝ ለሰነፎች ስድብ ከቶ አታድርገኝ የባሪያህን ጩኸት አቤቱ ስማኝ የነጻ ልቦና አምላኬ ሆይ አድለኝ በቃልህ ሰባብረው ድንጋዩን ልቤን ሕግን እንድፈፅም ስጠኝ ፍቃድህን ተስፋዬ ስለሆንክ ከማንም በላይ ወደ እኔ ተመልከት አምላክ አዶናይ ተስፋ ስላደረኩ አንተ አምላኬን የልመናዬም ድምጽ ይሰማ አሁን