ሃሌ ሉያ በሰማያት ላለው ዓለማትን ፈጥሮ ለሚገዛው እንዘምራለሁ እቀኝለታለሁ ጌትነቱን ክብሩን አደንቃለሁ ገናና ነው ክብርን የተመላ ድንቅ የሚያደርግ የለም ከእርሱ ሌላ ጉልበት ሁሉ ለስሙ ይሰግዳል ከአማልክት እርሱን ማን ይመስላል ልብሱ ዘርፍ መቅደሱ ተሞልቶ ስለክብሩ በገና ተቃኝቶ ምስጋናችን በእጣኑ ጢስ ሲያርግ ይመስጣል ያ የሰማዩን ሠርግ ሲቀኝለት ዳዊት በማኅሌት ቅዱስ ሲሉ ሱራፊል በኅብረት ከዙፋኑ ምሕረት ይታወጃል በምድራቸን ሰላም ፍቅር ይሰፍናል መሰወሪያው የእሳት ነበልባል ነው ሠረገላው ነፋስ ደመና ነው የእግዚአብሔር ስም የጸና ግንብ ነው ለሚፈሩት ኃይልና ብርታት ነው