እንደ አብርሃም እንሁን እንደሣራ/2/ እንግዳ እንቀበል በየተራ የተራበ እናብላ እንደአብርሃም የታረዘ እናልብስ እንደሣራ ለሥጋ ሳናስብ እንደአብርሃም እንጠቀም በነፍስ እንደሣራ አዝ --- የተጠሙ ይጠጡ እንደአብርሃም ይብሉ የተራቡ እንደሣራ እንደአብርሃም ቤት እንደአብርሃም ሥላሴ እንዲገቡ እንደሣራ አዝ --- ይህችን አጭር ዘመን እንደአብርሃም ካሁኑ ንቀን እንደሣራ እንግዳ እንቀበል እንደአብርሃም በድንካን ሆነን እንደሣራ አዝ --- እንደ አባቶቻችን እንደአብርሃም የዋሆች ሆነን እንደ ሣራ እንግዳ እንቀበል እንደ አብርሃም በማጠብ እግርን እንደ ሣራ