ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ/2/ ፈተና ቢገጠግመኝ ለበጎ ነው ብዬ አልፋለሁ/2/ በሠንሠለት አስረው በወኅኒ ቢጥሉኝ መከራን አብዝተው እጅግ ቢያስጨንቁኝ ለበጎ ነው ብዬ ተስፋ አድርጌሃለሁ ይሁን አንተ ያልከው እገዛልሃለሁ አዝ --- ትናንትናም ዛሬም አንተ ያው አንተነህ ፍቅርህ አይቀየር ወረትም የለብህ ስምህን መጥራቴ ሞገስ ይሆነኛል ጠላቴ ቢፎክር መቼ ያሸንፈኛል አዝ --- በመከራው ብዛት ጉልበቴ ደከመ ትካዜ ከብዶኛል ተስፋዬም ጨለመ ነገር ቢሆን ባይሆን አንተን እንዳከብር አድለኝ በጸጋ ጌታ የአንተን ፍቅር አዝ --- ከሀገር ተጥቼ በዱር መሠደዴ በባእዳን ሀገር ርቄ መሄዴ ለበጎ ነውና መቼ ይከፋኛል ፈጽሞ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ይይዘኛል አዝ ---