አትተወኝ አትጣለኝ/4/ ወድቄአለሁና ጌታ ሆይ አንሣኝ/2/ ቸሩ መድኃኒቴ የአልዓዛር ቤት እራት የኑሮዬ ጣእም የሕይወቴ መብራት በኃጢአት ጭቃ ላይ ወድቄአለሁና ጌዬ ሆይ አንሣኝ እጅህን ዘርጋና/2/ የሰጠኸኝ ክብር ይልጅነት ሥልጣን እንደ ሶምሶን ዝሙት ከደሊላ ጋራ አርቃኔን ቀረሁኝ ተላልፌ ሕግህን አምላኬ ዘርጋልኝ የምሕረት እጅህን/2/ ዘወትር እየበደልኩ ከሕግህ ርቄ በኃጢአት ጭቃ ላይ ክፉኛ ወድቄ በበደል እሥራት ተይዣለሁና አባቴ ሆይ ማረኝ መሐሪ ነህና/2/