ቸርነትህ ብዙ ምሕረትህ ብዙ በጉዞአችን ርዳን ጠባብ ነው መንገዱ ድንቅ ነው አምላክ ሆይ ፍቅርህ ለኛ ድንቅ ነው ለኛ አንተ ነህ መልካም እረኛ እስራኤል ወደቀ እስራኤል ተነሣ/2/ መንገድ አልቀናውም አምላኩን ቢረሣ/2/ የያእቆብን አምላክ እግዚአብሔርን ይዞ/2/ ምን እንዳተረፈ አውቆታል በጎዞ /2/ አዝ --- መንገዱ አይታክትም ጎዳናው የቀና /2/ እግዚአብሔር ከፊትም ከኋላም አለና /2/ እርሱ የሌለበት ቢመችም መንገዱ/2/ አቅጣጫው ወደ ሞት አይቀርም መውሰዱ/2/ አዝ --- በመንገድ ዝለን ወድቀን መቼ ቀርተናል/2/ የያእቆብ አምላክ ደግፎ አንስቶናል/2/ እግዚአብሔር ሲጠራን በቀደመው መንገድ/2/ ጉዞአችን ወዴት ነው በሞት ለመወሰድ/2/ አዝ --- አምላክ ሆይ ፍቅርህን በልባችን ሣለው /2/ እስከ ሞት በመስቀል የወደደን ማነው/2/ በበረሃው ጽናት ቢጸናብን ረሀቡ/2/ በረከት ሞላኸን ተረፈልን ምግቡ /2/ አዝ ---