ንዓ ንዓ አማኑኤል ንዓ ንዓ መድኃኔዓለም በፍሥሐ ወበሰላም ና ወደኛ መድኃኔዓለም/2/ ቅዱስ ጌታ አማኑኤል ቸር አምላክ መድኃኔዓለም ለእኛ ብለህ አማኑኤል ተሠቀልክ መድኃኔዓለም ልትባርከን አማኑኤል ና በሰርክ መድኃኔዓለም /2/ አዝ --- ሥጋህና አማኑኤል ደምህን መድኃኔዓለም ብሉ ብለህ አማኑኤል ሠጠኸን መድኃኔዓለም ሕይወትህ ሆኖ አማኑኤል አዳነን መድኃኔዓለም /2/ አዝ --- በኃጢአት ሞት አማኑኤል ወድቀን ሣለ መድኃኔዓለም ከጥንት ሀገር አማኑኤል ኑ አልከን መድኃኔዓለም ምንስ እንበል አማኑኤል ምን እናውራ መድኃኔዓለም ግሩም ብቻ አማኑኤል ያንተ ስራ መድኃኔዓለም/2/ አዝ ---