አዘክሪ ድንግል አዘክሪ ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን /2/ ካንቺ መወለዱን አዘክሪ በቤተልሔም አዘክሪ በጨርቅ መጠቅለሉን አዘክሪ መኝው ግርግም አዘክሪ ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን በዚያ በብርድ ወራት አዘክሪ የገበሩለትን አዘክሪ የአድግና የላም አዘክሪ እስትንፋሣቸውን አዘክሪ ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን በግብጽ በረሃ አዘክሪ መሠደድሽን አዘክሪ የአሸዋውን ግለት አዘክሪ ርሃቡና ጥሙን $ አዘክሪ ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን በመቃብሩ ዘንድ አዘክሪ ባነባሽው እንባ አዘክሪ አሳስቢ ድንግል ሆይ አዘክሪ ገነት እንድንገባ አዘክሪ ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን