ድንግል መከራሽን ጥቂት ላስሰው በሄሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው አንቺ የአምላክ እናት ደግሞም እመቤት እንደ ችግረኛ ተነሳሽ ስደት ኸረ ለመሆኑ እንዴት አለቀልሽ ስትንከራተቺ በረሃን አቆርጠሸ ይገሉታል ብለሽ ለልጅሽ አስበሽ በሔሮድስ ዘመን መከራሽን አየሽ /2/ አዛኝቷ ማርያም በጠራሁሽ ጊዜ እንድትደርሽልኝ በመከራ ጊዜ መከራን ያየ ሰው መቸም አይጨክንም አትጨክኝብኝ አደራሽን ማርያም /2/ የአማኑኤል እናት አንቺ መከረኛ እድሚሽን ጨረስሽው ሆነሽ ሐዘንተኛ መከራን ያየ ሰው መኟም አይጨክንም አትጨክኝብኝ አደራሽን ማርያም /2/