እመአምላክ ሙሽራ ነሽ ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ ኸኸ/3/ 12 ዓመት ቤተ መቅደስ የኖርሽ የመመረጥ ጸጋ ከጌታ ያገኘሽ አዝ --- በአብሣሪው መልአክ እጹብ ድንቅ ዜና ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና በ6ኛው ወር ተልኮ ገብርኤል ቤተመቅደስ ገባ ሊያበስራት ለድንግል አዝ --- በልዩ ሰላምታ ሰላም ለኪ አለሽ የክርስቶስ እናት በጣም ደስ ይበልሽ መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል ክብር ለአምላክ እናት ይድረሳት ይሉሻል አዝ --- በማሕፀንሽ ቢያድር የሠራዊት ጌታ ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ቅድስት ቦታ የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ ሰላም ላንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ አዝ ---