ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ የምጽናናበት ስምሽ ነውና ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር ለዘመናትም ስቸገር ስኖር ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ የዓለሙን መድኅን ወለድሽልኝ ካባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ በአሕዛብ ሀገር ስኖር ተሽጬ ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ ብቸኝነቴን አስረሻኝ ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ የምጽናናበት ስምሽ ነውና ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር ያሰብኩት ሃሳብ ደመና ሆኖ ቢበተንብኝ እንደ ጉም በኖ ይሆናል ያልኩት ሳይኖን ቢቀርም በእመአምላክ እኔ ተስፋ አልቆርጥም ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ የምጽናናበት ስምሽ ነውና ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና እናት አባቴ ባያስታውሱኝ ይህቺ ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ አንቺ ካለሺኝ ምን እሆናለሁ አውሎ ንፋሱን ባህሩን አልፋለሁ ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና ውለታሽ ድንግል አለብኝና ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ የምጽናናበት ስምሽ ነውና ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ አንቺን መውደዴን አያስተዉኝ በአሕዛብ መሀል ስምሸን ስጠራ መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና ውለታሽ ድንግል አለብኝና