እመቤቴ የአምላክ እናት ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት ለልጅሽም ክብር ወዳሴ ታቀርባለች ዘውትር ነፍሴ/4/ ልቤ ተነሣሣ ተቀኝ ለክበርሽ በፍጹም ትኅትና ሊያመሰግንሽ ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን የታጠረች ተክል እመብርሃን የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት የሰማይ የምድር ንግሥት ናትና ክብር ይገባሻል ዘወትር ጠዋት ማታ አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት በምልጃሽ አስቢኝ ኋላ ስራቆት ያንን የእሳት ባሕር አሻግረኝ ድንግል ሆይ እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ 937