የአዋጅ ነጋሪ ቃል በበረሀ አየለ የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳን ልባችን ለጌ መልካም መንገድ ይሁን የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም ዐውደ ዓመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና ካልተስተካከለ መንገድ የለምና የእግዚአብሔርን መንገድ እንጥረግ ሁላችን ማለፊያ እንዲሆነን ወደ አምላካችን አዝ . . . ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ ጽድቅና ርራኄ በእኛ ላይ ይስፋፋ ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል ሕይወት እንዲሆን አምላክ ተማጽነናል አዝ . . . ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን ከበደላችንም አንጻን አደራህ በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ አዝ . . .