የጠሩሽ አንቺን ተማጽነው የዳኑብሽ የበላኤ ሰብእ እመቤት የአምላክ እናት ድንግል አዛኝት ማርያም ቅድስት /2/ አዝ ---------- በቃል ኪዳንሽ ብዙዎች ድነዋል በምልጃሽ ጽድቅን አግኝተዋል የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል/2/ አዝ ----- የእሳት ባሕር በንቺ ተሻግረዋል ለሰማያዊው ክብር በቅተዋል/2/ አዝ ------- ነፍሳቸውም ጽድቅን አግኝታለች ሕይወታቸውም በአንቺ ትድናለች ድንግል ሆይ አትጣይኝ ትላለች/2/ አዝ ---------- እኔም በአንቺ እታመናለሁ የአምላክ እናት አሳስቢኝ እላለሁ በአማላጅነትሽ እድናለሁ/2/ አዝ ----------- እኛም በአንቺ እንታመናለን የአምላክ አሳስቢ እንላለን በአማላጅነትሽ እንድናለን;2/ አዝ ----------- ምእመናንም በአንቺ ያምናሉ የአምላክ እናት አሳስቢ ይላሉ በአማላጅነትሽ ይድናሉ/2/ አዝ ------------