አንቲ ዘበአማን /2/ ረከብኪ ጸጋ ክብረ ድንግል /2/ የአቢ ክብራ ለማርያም በይ እንግዲ ድንግል ዘበአማን ከእኛ አትሽሺ ዘበአማን የክርስቲያኑን ልብ ዘበአማን ትኅትናን አልብሺ ያሬድ ጸናጽል ዘበአማን የዘወትር ቅዳሴ - የአባሕርያቆስ ዘበአማን የዘወትር ቅሳሴ -- ርኅርኂተ ኅሊና ዘበአማን የሐዋርያ ሞገስ --- የመላእክት እህት ዘበአማን ማኅደረ ሥሉስ ሥሉስ ቅዱስ ተብሎ ዘበአማን የሚመሰገነው - የፍጥረታት ገዥ ዘበአማን የአንቺ ልጅ እኮ ነው - የምታምሪ ርግብ ዘበአማን ሰላምን ያስገኘሽ ዘበአማን ንጽሕናሽን አይቶ ዘበአማን ወልድ መረጠሸ አትርሺኝ ድንግል ሆይ ዘበአማን እኛ ልጆችሽን ከአምላክ አስታሪቂን ዘበአማን እኛ ደካሞችን ስለ በደላን ዘበአማን ችላ ሳትይን ዘበአማን ምሕረት አሠጪን ዘበአማን ድንግል አትርሺን የመመኪያችን ዘውድ ዘበአማን እመብርሃን ከልጅሽ አስታሪቂኝ ዘበአማን እንዳንቀር ወድቀን