ትውልድ ሁሉ የሚማጸኑሽ በመላእክት የተመሠገንሽ ክብር አክሊሌ ሰላም ልበልሽ ትውልድ ሁሉ ዓለም ሣይፈጠር ትውልድ ሁሉ በለምጽ የነደደው ይቀደስ ከንፈሬ እንደ አባ ጊዬርጊስ ላምስግንሽ ክብሬ ዓይኖቼ ይታገሉ ለውዳሴሽ ቀለም የክርስቶስ እናት የመድኃኔዓለም ትውልድ ሁሉ አንቺን ለመዘከር ይትጋ ኅሊናዬ በውዳሴሽ ቅኔ ይሙላ ልቡናዬ ልቀበል በረከት ስምሽን ጠርቼ አንቺ ባለሽበት ይቁሙ እግሮቼ